ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ኤፌ 1፡3

WELCOME TO YM ወደ ሥላሴ ማኅበር እንኳን በደህና መጡ፡፡

የሥላሴ ማኅበር

YESLASE MAHBER

“እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።” ዮሐ.17:22-23

የሥላሴ ማኅበር

ወደ ሥላሴ ማኅበር እንኳን በደህና መጡ፡፡ የሥላሴ ማኅበር በእግዚአብሔር አስገራሚ ፍቅር ተማርከንና ተሸንፈን ወደሰማያዊው ቤተሰብ ውስጥ የገባን ሰዎች ማኅበር ሲሆን እርስዎም በዚህ ፍቅር ተማርከው ከኛ ጋር ኅብረት ይኖሮዎት ዘንድ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። 1. ዮሐ. 1:3

የሥላሴ ማኅበር መሠረቱ በሰማይ ነው፡፡ የሥላሴ ማኅበር ሰማያዊ ነው፡፡ በአካል ሶስት በመለኮት አንድ የሆነው ሥሉስ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰውን ሲፈጥረው በራሱ መልክ ነው፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ አንድን ስናነብ እግዚአብሔር ሁሉን እንደወገኑ ፈጠረ እንዲህ እንዲህ እናነባለን፡፡ “እግዚአብሔርም አለ፦ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።” ዘፍ።1፤24-25 እያለ ይተርክልንና ሰው ላይ ሲደርስ “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።” ይላል፡፡ ዘፍ።1፤26-27 ሁሉን እንደወገኑ ከፈጠረ በኋላ ሰውን ደግሞ እንደ ወገኑ ማለትም በራሱ ወገን በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ፈጠረው፡፡ ይህም ታላቅ ክብር ሲሆን ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት እንዲያደርግ የእግዚአብሔር ቤተሰብ እንደሆነ ያሳየናል፡፡ ሰው በውድቀት ምክን ያት ከዚህ ኅብረት ተለይቶ የነበረ ቢሆንም በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ ወደዚህ ኅብረት መመለሱን ቅዱሳን ሐዋርያት እንዲህ በማለት ይመሰክሩልናል፡፡ “እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።”

ሰማያዊ ወደሆነው ወደዚህ ቤተሰብ ወደ ሥላሴ ማኅበር እንኳን በደህና መጡ፡፡

” ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።”

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:1-4

*የሥላሴ ማኅበር የቀደመውን አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ሐዋርያት የሰበኩትን የጌታችንንና የመድኃኒታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ብቻ የሚሰብክና የኢየሱስ ክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ትታነጽ ዘንድ የሚተጋ  ማኅበር ነው፡፡  በመሆኑም በዚህ ድኅረ ገጽ የሚቀርቡት መልእክቶች እና ትምህርቶች ሁሉ የሥላሴን ማኅበር አገልግሎት ብቻ የሚወክሉ ብቻ መሆናቸውን በትህትና እናሳውቃችኋለን፡፡

እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ። ኢሳ 2፡5

ከሌሎች ወንድሞችና እህቶች ጋር የቃሉን ወተት እየጠጡ ደቀ መዝሙር ለመሆን ወደ ሚያድጉበት ህብረት ይቀላቀሉ፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ስለ መጀመሪያው ዘመን ክርስቲያኖች ሲናገር “በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።” ይላል፡፡ ሐዋ 2፡42 ፡ ዛሬም ከሌሎች ወገኖች ጋር ቃሉን ለመስማትና የበለጠ ለመቀራረብ እንዲያስችለን ይህንን ጠንከር ያሉ መልእክቶችን የምንሰማበትን እድል አዘጋጅተናል፡፡ ለመመዝገብ የምትከፍሉት ይህንን ዌብሳይት ለማዘጋጀት የሚረዳ ሲሆን እግዚአብሔር በየጊዜው የሚያስተምረንን መልእክቶች በማግኘትም መታነጽና ማደግ ይሆንልናል፡፡

ጦማር

በላስ ቤጋስ የሚኖሩ ቅዱሳን ምስክርነት

የትንሣኤው ሚስጥርና ኃይል  ክፍል አንድ 

የትንሣኤው ሚስጥርና ኃይል  ክፍል ሁለት

የትንሣኤው ሚስጥርና ኃይል  ክፍል ሶስት

የማለዳ ጠል

የፍቅር ስጦታ Love gift

ZELLE

281-745-4435

በዩቱብ ቻናላችን ያሉ የቢዲዮ መልእክቶች

የእግዚአብሔር ፍቅር

የማለዳ ጠል

ስለ ሕይወት ቃል

አገልግሎታችንን ለብዙዎች እንዲደርስ ልብዎ የፈቀደውን ይደግፉ፡፡