የሥላሴ ማኅበር
YESLASE MAHBER
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የምንሰበሰብ የእግዚአብሔር ልጆች የመንፈስ ማረፊያ እና የሰማያዊ ቤተሰብ ቤት።
A sanctuary of Rest and fellowship of God's children, gathered together under the name of the Father, the Son, and the Holy Spirit
ራዕይና ተልዕኮ • VISION & FELLOWSHIP
የሰማያዊው ቤተሰብ ኅብረት
Home of the Heavenly Family
ወደ ሥላሴ ማኅበር እንኳን በደህና መጡ፡፡ የሥላሴ ማኅበር በእግዚአብሔር አስገራሚ ፍቅር ተማርከንና ተሸንፈን ወደሰማያዊው ቤተሰብ ውስጥ የገባን ሰዎች ማኅበር ሲሆን እርስዎም በዚህ ፍቅር ተማርከው ከኛ ጋር ኅብረት ይኖሮዎት ዘንድ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡ ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። ፩. ዮሐ. ፩፥፫
የሥላሴ ማኅበር መሠረቱ በሰማይ ነው፡፡ የሥላሴ ማኅበር ሰማያዊ ነው፡፡ በአካል ሶስት በመለኮት አንድ የሆነው ሥሉስ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰውን ሲፈጥረው በራሱ መልክ ነው፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ አንድን ስናነብ እግዚአብሔር ሁሉን እንደወገኑ ፈጠረ እንዲህ እንዲህ እናነባለን፡፡ “እግዚአብሔርም አለ፦ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።” ዘፍ።፩፤፳፬-፳፭ እያለ ይተርክልንና ሰው ላይ ሲደርስ “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠраቸው።” ይላል፡፡ ዘፍ።፩፤፳፮-፳፯ ሁሉን እንደወገኑ ከፈጠረ በኋላ ሰውን ደግሞ እንደ ወገኑ ማለትም በራሱ ወገን በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ፈጠረው፡፡ ይህም ታላቅ ክብር ሲሆን ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት እንዲያደርግ የእግዚአብሔር ቤተሰብ እንደሆነ ያሳየናል፡፡ ሰው በውድቀት ምክንያት ከዚህ ኅብረት ተለይቶ የነበረ ቢሆንም በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ ወደዚህ ኅብረት መመለሱን ቅዱሳን ሐዋርያት እንዲህ በማለት ይመሰክሩልናል፡፡ “እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።”
ሰማያዊ ወደሆነው ወደዚህ ቤተሰብ ወደ ሥላሴ ማኅበር እንኳን በደህና መጡ፡፡
The Trinity Fellowship is a community of people who have been captivated and overwhelmed by God’s amazing love and have entered into the heavenly family. We invite you with great love to be captivated by this love and have fellowship with us. Our fellowship is with the Father and with His Son, Jesus Christ. 1 John 1:3
The foundation of the Trinity Fellowship is in heaven. The Trinity Fellowship is heavenly. When the Triune God, who is three in person and one in divinity, first created man, He created him in His own image. When we read Genesis chapter one, we read that God created everything according to its kind. “And God said, ‘Let the earth bring forth living creatures according to their kinds—livestock and creeping things and beasts of the earth according to their kinds.’ And it was so. And God made the beasts of the earth according to their kinds and the livestock according to their kinds, and everything that creeps on the ground according to its kind. And God saw that it was good.” Genesis 1:24-25. Then, when it comes to man, it says, “Then God said, ‘Let us make man in our image, after our likeness. And let them have dominion over the fish of the sea and over the birds of the heavens and over the livestock and over all the earth and over every creeping thing that creeps on the earth.’ So God created man in his own image, in the image of God he created him; male and female he created them.” Genesis 1:26-27. After creating everything according to its kind, He created man according to His own kind, that is, in His own kind, in the image and likeness of God. This is a great honor and shows us that man is a family of God, to have fellowship with God. Although man was separated from this fellowship because of the fall, the holy apostles testify that through the saving work of Jesus Christ, man has been returned to this fellowship, saying, “that which we have seen and heard we proclaim also to you, so that you too may have fellowship with us; and indeed our fellowship is with the Father and with his Son Jesus Christ.”
Welcome to this heavenly family, the Trinity Fellowship