God is faithful

እግዚአብሔር የታመነ ነው

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።” መዝሙረ ዳዊት 46፥10

በመምህር ጸጋ

ዕረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ

እግዚአብሔርን በማወቅና በማመን የሚገኝ እረፍት፡፡ 

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። መዝሙረ ዳዊት 46፥10 

ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። እብ 11፡11

በእግዚአብሔር ስለምናምን ነው በተስፋው የምናምነው፡፡ ይህም ማለት ተስፋውን ከማመናችን በፊት የተናገረውን አምላክ ነው ያመነው፡፡ ከንግግሩ በፊት ተናጋሪውን ነው ያመነው ወይም በንግግሩ ተናጋሪውን ነው ያመነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ተናጋሪውን እግዚአብሔርን አውቀንና አይተን እንድናምን ነው የተጻፈልን፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በመጀመሪያ በእግዚአብሔር እንድናምን ነው የሚያደርገን፡፡ እግዚአብሔር የታመነ ነው የምንለው የሚያደርገውን ካየን በኋላ አይደለም፡፡ ራሱን ተናጋሪውን ማንነቱን ኃይልነቱን ታማኝነቱን ነው የምናምነው፡፡ በሥራው የምንመዝነው ከሆነ አንድ ነገር እስኪያደርግ ጠብቀን በዚያ ድርጊት በመረታት ነው የምናምነው፡፡ ይህ ግን እምነት አይደለም፡፡ እምነት ከማይታየው ይጀምራልና፡፡ እግዚአብሔርን የምናምነው ማንነቱ አምላክነቱ አባትነቱ በርቶልን ነው፡፡ እምነት ከብርሃን ከመገለጥ ነው የሚጀምረው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰወረውን አብ ብቻ የሚያውቀውን የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት አወቀ አመነም፡፡ አንተ ክርስቶስ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።” አለው ማቴ 16፤16 እና 17

በእግዚአብሔር ማመን ማለት በአባት ወይም በእናት ክንድ ታቅፎ ወይም ታዝሎ መተኛት ማለት ነው፡፡ አንድ ህጻን ታቅፎ ወይም ታዝሎ ሲተኛ ማንነቱን ሁሉ ለእናቱ ወይም ለአባቱ አሳልፎ ሰጥቶአል፡፡ እርሱ አይሰማም ራሱን አይከላከልም እነርሱ ግን ያቅፉታል ይንከባከቡታል፡፡ በዚህ ሰዓት የሚሆነውን ሁሉ አያውቅም አያይም ነገር ግን በምቾት ተኝቶአል፡፡ እግዚአብሔርን ስናውቅ በርሱ ላይ እናርፋለን፡፡

እምነት በእምነት መንፈስ አማካኝነት የማይታየውን እግዚአብሔርን አይቶ በታየው ማንነቱ በእግዚአብሔርነቱ ማመን ነው፡፡ ይህም በእግዚአብሔር በራሱ ላይ እርፍ እንድልን ይረዳናል፡፡ በእግዚአብሔር ማመን ማለት በአባት ወይም በእናት ክንድ ታቅፎ ወይም ታዝሎ መተኛት ማለት ነው፡፡ አንድ ህጻን ታቅፎ ወይም ታዝሎ ሲተኛ ማንነቱን ሁሉ ለእናቱ ወይም ለአባቱ አሳልፎ ሰጥቶአል፡፡ እርሱ አይሰማም ራሱን አይከላከልም እነርሱ ግን ያቅፉታል ይንከባከቡታል፡፡ በዚህ ሰዓት የሚሆነውን ሁሉ አያውቅም አያይም ነገር ግን በምቾት ተኝቶአል፡፡ እግዚአብሔርን ስናውቅ በርሱ ላይ እናርፋለን፡፡ ህይወታችንን ሁሉ በእጆቹ ላይ አስቀምጠን እንኖራለን፡፡ እረፍት የምናገኘው እርሱን በማወቅና በርሱ ላይ በማረፍ እንጂ በሚያደርግልን ድርጊቶች አይደለም፡፡ እረፍታችንም ማረፊያችንም እርካታችንም መርኪያችንም እርሱ ነው፡፡ ሰላም ሰጪያችንም ሰላማችንም እርሱ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እምነት ማለት እግዚአብሔር ወደፊት እንዲህ ያደርግልኛል ያን ጊዜ አርፋለሁ እደሰታለሁ ብሎ ማሰብ ይመስለናል፡፡ እምነት ግን እግዚአብሔርን ራሱን ማመን ነው፡፡ እርሱን ራሱን ማመን ከሆነ ደግሞ ቀጠሮ አንሰጥም እርሱ ዛሬና አሁን ነውና፡፡ እርሱ አልፋና ኦሜጋ ዘላለማዊ ነውና አሁን በርሱ እናርፋለን፡፡

የአባት ፍቅር

ከዚህ በታች ያለውን የወንጌል ድምጽ እንዲሰሙ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡

 ሣራ ያመነችው ከጸነሰች ወይም ከወለደች በኋላ አይደለም፡፡ ሣራ በመጀመሪያ ያመነችው የተስፋ ቃሉን ሳይሆን የተስፋ ቃል የሰጠውን እግዚአብሔርን ራሱን ነው፡፡ ተስፋን የሰጠውን እግዚአብሔርን ስላመነች ከዚያ በመነሳት የሰጠውን ተስፋ አመነች ተቀበለችም፡፡ የተሰጣት ተስፋ ከታመነ አምላክ የመጣ ነውና አመነችው፡፡   

እግዚአብሔር ራሱ የታመነ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አሜን ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ  ም እመናን በጻፈው መልእክቱ 

ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው። 1 ቆሮ 1፡9 ይላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ራሱ የታመነ ነው፡፡ ማንነቱ የታመነ ነው፡፡ በታመነው ማንነቱ ስንታመን ምእመናን እንባላለን፡፡ 

አሜን ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

Leave a Comment