his great love

የእግዚአብሔር ፍቅር

“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

Greater love hath no man than this, that a man lay down his life for his friends.” ዮሐንስ 15:13

በመምህር ጸጋ

ክርስቲያን የሆናችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ለምን ክርስቲያን እንደሆናችሁ ቆም ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ወላጆቻችሁ ክርስቲያኖች ሆነው ስለቆዩና የነርሱን ፈለግ እንዲሁ ስለተከተላችሁ ነው? ወይስ ከሞት በኋላ የምትሄዱበት ስለሚያሳስባችሁ ነው? ወይስ ሌላ? ብዙዎች ስለምን ክርስቲያን እንደተባሉ የማያውቁ አሉ፡፡ ብዙዎች ደግሞ ከሞት በኋላ የሚመጣውን ፍርድ በመፍራት ሃይማኖተኛ የሆኑ አሉ፡፡ እውነተኛው ክርስትና ግን የትክክለኛ ጋብቻን ሁኔታ ይመስላል፡፡ ባልና ሚስትን ወደባልና ሚስትነት የሚያመጣቸው ብቸኛ ምክንያት በመካከላቸው የሚፈጠረው የፍቅር መሳሳብ ነው፡፡ እግዚአብሔርም እኛን ወደራሱ መሳብ የሚፈልገውና የሳበው በፍቅሩ ኃይል ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የፍቅር መልእክት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ፍቅር ቆሞ ሲሄድ ማለት ነው፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅር አካል መሆን ሰው መሆን ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥና ሲወለድ የእግዚአብሔር ፍቅር ተገለጠ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እኛን ወደራሱ የሚስብበት የፍቅር እጅ ነው፡፡ በዚህ ፍቅር በሆነ ጌታ ስንያዝና ስንነካ ወደ እግዚአብሔር እንሳባለን፡፡ ክርስቶስንም ለብሰን ክርስቲያን እንባላለን፡፡ አንድ ላይ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን እንባላለን፡፡ ወንድሞቼና እህቶቼ በዚህ ፍቅር ተስባችሁ ነው ክርስቲያኖች የሆናችሁት? ጥያቄው ባልና ሚስትን በምን ምክንያት ተጋባችሁ? ብሎ እንደመጠየቅ ነው፡፡ እውነተኛ ባልና ሚስት በፍቅር ምክንያት ነው፤ ተዋደን ነው፤ ወድጃት ነው፤ ወድጀው ነው ማለታቸው አይቀርም፡፡ መቸም ብዙዎቻችን ከዚህ የተለየ መልስ ከባልና ሚስት አንጠብቅም፡፡ ይህ ሲባል ግን በዚህች በኃጢአት በወደቀች ዓለም ከዚህ ውጭ በሆኑ ምክንያቶች የሚመሰረት ጋብቻ የለም ማለት አይደለም፡፡ በተለያየ ምክንያት ሰዎች በፍቅር ያልተመሰረተ ጋብቻ ይኖራቸዋል፡፡ ይህም የተለያየ ሥጋዊ ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ በፍቅር ላይ ያልተመሰረተ ከዚህም በባሰ ሁኔታ በጠለፋ ማለትም ሴትን  ልጅ ያለ ፈቃድዋ አስገድዶ የማግባት ልማዶችም አሉ፡፡

ባልና ሚስትን ወደባልና ሚስትነት የሚያመጣቸው ብቸኛ ምክንያት በመካከላቸው የሚፈጠረው የፍቅር መሳሳብ ነው፡፡ እግዚአብሔርም እኛን ወደራሱ መሳብ የሚፈልገውና የሳበው በፍቅሩ ኃይል ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር የፍቅር መልእክት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ፍቅር ቆሞ ሲሄድ ማለት ነው፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅር አካል መሆን ሰው መሆን ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥና ሲወለድ የእግዚአብሔር ፍቅር ተገለጠ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እኛን ወደራሱ የሚስብበት የፍቅር እጅ ነው፡፡ በዚህ ፍቅር በሆነ ጌታ ስንያዝና ስንነካ ወደ እግዚአብሔር እንሳባለን፡፡ ክርስቶስንም ለብሰን ክርስቲያን እንባላለን፡፡ አንድ ላይ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን እንባላለን፡፡

እግዚአብሔር ጋብቻን የመሰረተው በፍቅር መሠረት ላይ ቢሆንም ሰዎች በኃጢአት በመውደቃቸው ምክንያት እነዚህ ሁሉ የተሳሳቱ ግንኙነቶች ሲደረጉ እናያለን፡፡ ዋና መልእክታችን ስለ ምድራዊው የጋብቻ ሥርዓት ለመናገር ሳይሆን ይህንን እንደ ምሳሌ በመጠቀም ከእግዚአሔር ጋር ስለሚኖረን ግንኙነት ለመመልከት ነው፡፡ ሰዎች የተሳሳተ እና ፍቅር የሌለው ግንኙነት የሚመሰርቱት በፍጥረታዊው ዓለም ብቻ ሳይሆን በክርስትና ህይወታቸውም ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ያልሆነ ግንኙነት ይመሰርታሉ፡፡ ከላይ በፍጥረታዊው ጋብቻ ከፍቅር ውጭ በሆነ መንገድ የሚመሰረቱት ጋብቻዎች ሁሉ ትክክል እንዳልሆኑ አይተናል፡፡ እንደዚሁም በመንፈሳዊው ዓለም የተሳሳተ ወንጌልን በሚሰብኩ ሰዎች ምክንያት ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተሳሳተ መሰረት ላይ ይመሰርታሉ፡፡ እነዚህ ሐሰተኛ ሰባኪዎች ግማሾቹ ወደኛ ብትመጡ እግዚአብሔር ይህን ያደርግላችኋላ ይህን ይሰጣችኋል እያሉ ሰዎች ለሥጋዊ ጥቅም ብለው እንዲመጡ ይሰብካሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ እግዚአብሔር በጣም የሚያስፈራ የሚቀጣ ፈራጅና ጨካኝ አምላክ መሆኑን በመናገር ወደርሱ ካልመጣን እንዴት እንደሚቀጣን እያስፈራሩ ወደርሱ እንድንቀርብ ይጨቀጭቁናል፡፡ ወንጌል እግዚአብሔር እንደሚባርክ እንዲሁም እንደሚፈርድና እንደሚቀጣ ቢናገርም ነገር ግን በዚህ አስፈራርቶ ወደርሱ እንድንመጣ አይደለም ይህን  የሚናገረው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በፍቅር ነው ወደራሱ የሳበው፡፡ በፍቅሩ ለመሳብ እና ወደርሱ ለመምጣት ፈቃደኛ ያልሆኑት ግን ፍቅሩን ስለገፉ መጨረሻቸው ከርሱ መለየትና መራቅ ስለሆነ ይህ ትልቅ ፍርድ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርዱ ፍቅሩን የመግፋታቸው ውጤት እንጂ ፈርተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመጡ ለማድረግ የተሰጠ ማስፈራሪያ አይደለም፡፡ የሐሰተኛ መምህራንን እና ሰባኪዎችን ወንጌል የሚሰሙት ሰዎችም አንዳንዱ ከጥቅም አንጻር ማለትም ፍጥረታዊ በረከት ለማግኘት ወይም ሲሞት የወርቅ ቢላ ለመውረስ ሲሆን ሌላው ደግሞ ከሞት በኋላ ወደ ሲኦል እንዳይሄድ በመፍራት ክርስቲያን ነኝ ይላል፡፡ ይህ ከላይ እንዳየነው በጠለፋና በጥቅም ከሚመሰረት ጋብቻ ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ማንንም ሰው አስገድዶ አስፈራርቶ ወይም በጥቅም አባብሎ ወደርሱ እንዲመጣ አይፈልግም፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ማሸነፍ የፈለገው በፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡

ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም

ከዚህ በታች ያለውን የወንጌል ድምጽ እንዲሰሙ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡

Play Video

ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም ክፍል ሁለት


ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

Greater love hath no man than this, that a man lay down his life for his friends.

 

Play Video

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐስን ይህንን እግዚአብሔር የተገለጠበትን የፈቅር መንገድ ሲተንትን እንዲህ ይለናል፡፡ አስተውለን እናንብበው፡፡

1 ዮሐ 4 

7 ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።

8 ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።

9 በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።

10 ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።

11 ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።

12 እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።

13 ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን።

14 እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።

15 ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

16 እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።

17 በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።

18 ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።

19 እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።

20 ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

21 እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።

ወንድሞቼና እህቶቼ እውነተኛው የእግዚአብሔር መንገድ ይህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ለማሸነፍ የተገለጠው በፍቅር ነው፡፡ በቅዱሳን መላእክት ተከቦ ለዘለዓለም ሲመሰገን የሚኖረው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ባዶ አድርጎ ያለምንም አጃቢ ደካማ ሆኖ የመጣው በፍቅሩ እኛን ለመሳብና ለመማረክ ነው፡፡ 

በሥላሴ ማኅበር ይህንን የእግዚአብሔርን የፍቅር ወንጌል እንቆርሳለን እንካፈላለን፡፡ ይህም መልእክት በማሕበራችን ከምንካፈላቸው ትምህርቶች አንዱ ነው፡፡ እርስዎም ይህን የፍቅር ማዕድ ከኛ ጋር ለመካፈል የሚወዱ ከሆነ ከዚህ በታች ያለውን ፎርም ሞልተው ይላኩልን ከኛም ይሰማሉ፡፡

እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ፡፡

Registration free

Join Us

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *