የሥላሴ ማኅበር
ወደ ሥላሴ ማኅበር እንኳን በደህና መጡ፡፡ የሥላሴ ማኅበር በእግዚአብሔር አስገራሚ ፍቅር ተማርከንና ተሸንፈን ወደሰማያዊው ቤተሰብ ውስጥ የገባን ሰዎች ማኅበር ሲሆን እርስዎም በዚህ ፍቅር ተማርከው ከኛ ጋር ኅብረት ይኖሮዎት ዘንድ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። 1. ዮሐ. 1:3
የሥላሴ ማኅበር መሠረቱ በሰማይ ነው፡፡ የሥላሴ ማኅበር ሰማያዊ ነው፡፡ በአካል ሶስት በመለኮት አንድ የሆነው ሥሉስ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰውን ሲፈጥረው በራሱ መልክ ነው፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ አንድን ስናነብ እግዚአብሔር ሁሉን እንደወገኑ ፈጠረ እንዲህ እንዲህ እናነባለን፡፡ “እግዚአብሔርም አለ፦ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።” ዘፍ።1፤24-25 እያለ ይተርክልንና ሰው ላይ ሲደርስ “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።” ይላል፡፡ ዘፍ።1፤26-27 ሁሉን እንደወገኑ ከፈጠረ በኋላ ሰውን ደግሞ እንደ ወገኑ ማለትም በራሱ ወገን በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ፈጠረው፡፡ ይህም ታላቅ ክብር ሲሆን ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት እንዲያደርግ የእግዚአብሔር ቤተሰብ እንደሆነ ያሳየናል፡፡ ሰው በውድቀት ምክን ያት ከዚህ ኅብረት ተለይቶ የነበረ ቢሆንም በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ ወደዚህ ኅብረት መመለሱን ቅዱሳን ሐዋርያት እንዲህ በማለት ይመሰክሩልናል፡፡ “እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።”
ሰማያዊ ወደሆነው ወደዚህ ቤተሰብ ወደ ሥላሴ ማኅበር እንኳን በደህና መጡ፡፡
” ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።”
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:1-4
*የሥላሴ ማኅበር የቀደመውን አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ሐዋርያት የሰበኩትን የጌታችንንና የመድኃኒታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ብቻ የሚሰብክና የኢየሱስ ክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ትታነጽ ዘንድ የሚተጋ ማኅበር ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ድኅረ ገጽ የሚቀርቡት መልእክቶች እና ትምህርቶች ሁሉ የሥላሴን ማኅበር አገልግሎት ብቻ የሚወክሉ ብቻ መሆናቸውን በትህትና እናሳውቃችኋለን፡፡
የእግዚአብሔር ፍቅር
ተከታታይ መልእክቶች
መልእክተ ዮሐንስ የተባለው ጉባኤያችን ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፋቸው መል እክቶቹ ሁሉ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያ የነበረውን በማወቅና በማመን ሊያድጉ ለሚፈልጉ ም እመናን የተዘጋጀ ትምህርት የሚሰጥበት ነው፡፡ ይህ ጉባኤ የሚደረገው በየሳምንቱ ቅዳሜ በቴክሳስ ሰዓት ከ 1:30-2:30 PM በ Zoom አማካኝነት የሚደረገ ጉባኤ ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ የክርስትናችን መሠረት የሆነውን ሚስጢረ ሥጋዌን እና ሚስጢረ ተዋሕዶን እንደዚሁም መሠረታዊ ነገረ ድኂንን እንማራለን፡፡ በዚህ ጉባኤ ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ሁሉ ፎርሙን ሞልታችሁ ብትልኩልን በሞላችሁት አድራሽ መሠረት አግኝተናችሁን እንዴት እንደምትጀምሩ የበለጠ ማብራሪያ እንሰጣችኋለን፡፡ ሁላችሁም ፎርሙን በመሙላት የመልእክተ ዮሐንስ ጉባኤያችንን እንድትቀላቀሉና የሕይወትን ቃል እንድትመገቡ በታላቅ ፍቅር እንጋብዛችኋለን፡፡ እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ፡፡ የሥላሴ ማኅበር፡፡
ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1፡1-4
የማለዳ ጠል
የሥላሴ ማኅበር ማኅበርተኛና ደጋፊ ይሁኑ፡፡
ገንዘባችንን ለእግዚአብሔር የምንሰጥበት ትክክለኛ መንገድና ምክንያት፡፡
ለእግዚአብሔር ቤትና ለወንጌሉ ሥራ ገንዘባችንን የምንሰጠው ለመጽደቅ ሳይሆን ስለጸደቅን ነው፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ የሞተልን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ምንም የጽድቅ ሥራ ሳናደርግ መሆኑ ጽድቅን የምናገኘው በራሳችን ሥራ አለመሆኑን ያሳየናል፡፡ ስለዚህ ለወንጌሉ ሥራ ገንዘብ የምንሰጠው ጽድቅን ለመሸመት ሳይሆን በፍቅሩ ያሸነፈን ክርስቶስ ለሌሎችም እንዲሰበክ ነው፡፡ ይህ ሚስጢር ሲገባን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ደስታ ነው የምንሰጠው፡፡ ትክክለኛውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመስጠት ህይወት ለመረዳት ይህንን አጭር ቢዲዮ ይስሙ ዘንድ በፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡