It is of the Lord’s mercies that we are not consumed, because his compassions fail not. ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።

የእግዚአብሔር ምሕረትና ርህራሄ

“ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።” ሰቆቃወ ኤርሚያስ 3፡22

በመምህር ጸጋ

የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን በዘረጋ ጊዜ እግዚአብሔር ስለ ክፉው ነገር አዘነ፥ ሕዝቡንም የሚያጠፋውን መልአክ፦ እንግዲህ በቃህ እጅህን መልስ አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ነበረ። 2 ሳሙ 24፥16 

እግዚአብሔር ሆይ በመልክህ ለፈጠርከው ልጅህን ኢየሱስ ክርስቶስን እስከ መስጠት ለወደደከውም የሰው ልጅ ራራ፡፡ እርስ በርስ ከመተላለቅ አድነኸው በወንጌልህ ብርሃን ወደ ራስህ መልሰው፡፡

እርሱ ግን መሓሪ ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም።መዝሙረ ዳዊት 78፥38 

አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ምሕረትህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።  መዝሙረ ዳዊት 86፥5 

አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ መዓትህ የራቀ ምሕረትህም እውነትህም የበዛ፤ መዝሙረ ዳዊት 86፥15 

እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ።መዝሙረ ዳዊት 103፥8

የአባት ፍቅር

ከዚህ በታች ያለውን የወንጌል ድምጽ እንዲሰሙ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡

ለተአምራቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው።መዝሙረ ዳዊት 11፥4 

ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ መሓሪና ይቅር ባይ ጻድቅም ነው። መዝሙረ ዳዊት 112፥4

እግዚአብሔር መሓሪና ጻድቅ ነው፥ አምላካችንም ይቅር ባይ ነው። መዝሙረ ዳዊት 116፥5 

መሓሪዬና መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና መድኃኒቴ፤ ረዳቴና መታመኛዬም፤ ሕዝቤንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ። መዝሙረ ዳዊት 144፥2 

እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነውመዝሙረ ዳዊት  145፥8

Leave a Comment