My heart said unto thee ልቤ አንተን አለ

የእግዚአብሔር ፍቅር

“አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።” መዝ 27:8

በመምህር ጸጋ

ልባችን አጥብቆ የሚሻው ምንድን ነው? ልባችን እጅግ የሚፈልገው  ማንን ነው? ከልባችን አጥብቀን የምንፈልገው እግዚአብሔርን ካልሆነ አምላካችን እርሱ አይደለም፡፡ ብዙዎቻችን እግዚአብሔርን የምንፈልገው ልባችን  በርሱ ፍቅር ተስቦና ተማርኮ የርሱን ፊት ለማየት ናፍቀን ሳይሆን አንድ የምንፈልገውን ነገር እንዲያደርግልን ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ እግዚአብሔርን ስንፈለገው በእውነት እርሱን እየፈለግ ነው ሳይሆን በርሱ አማካኝነት የርሱን ሁሉን ቻይነት ተጠቅመን ልባችን እጅግ የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት ነው፡፡

እግዚአብሔርን እንደ መንገድ ተጠቅመን ሌላ ነገር ለማግኘት የምናምነው ከሆነ እውነተኛው አምላካችን እርሱ ሳይሆን ያ በርሱ በኩል አድርገን ልናገኘው የፈለግነው ነገር ነው የሚሆነው፡፡

እርሱን እንደ መንገድ ተጠቅመን ሌላ ነገር ለማግኘት የምናምነው ከሆነ እውነተኛው አምላካችን እርሱ ሳይሆን ያ በርሱ በኩል አድርገን ልናገኘው የፈለግነው ነገር ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የበለጠ ስፍራን ሰጥተነዋልና፡፡ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ “ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት።” የቅዱስ ማርቆስ ወንጌል 12፡29-30

የአባት ፍቅር

ከዚህ በታች ያለውን የወንጌል ድምጽ እንዲሰሙ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡

Play Video

ስለዚህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችን በፍጹም ነፍሳችን በፍጹም ሐሳባችን ከወደድነው ከርሱ አልፈን የምንወደው ነገር የለንም፡፡ እርሱ የልባችን ጉዞ ፍጻሜ የጉዞአችን መጨረሻ የእርካታችን ጣሪያ የህይወታችን መድረሻ ነው፡፡ በዚህ ፍቅር የምትወዱት ከሆነ እግዚአብሔር መተላለፊያና መሸጋገሪያችሁ ሳይሆን መድረሻችሁ ይሆናል፡፡ እርሱን የምንፈልገው በርሱ በኩል አንድ ነገር ለማግኘት ሳይሆን እርሱን ለማግኘት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንዳለው “ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ” እንለዋለን፡፡

እግዚአብሔር ልባችንን ወደርሱ ያቅና አሜን፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *