The Oneness of the Spirit የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት

የእግዚአብሔር ፍቅር


“ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።” 1. ዮሐንስ 1:7-8

 

በመምህር ጸጋ

የክርስቶስ ኢየሱስ አካል የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እጅግ ሚስጢራዊና ሰማያዊ ሙሽራ ናት፡፡ በዚህ መል እክት የዚህችን አስደናቂ ሙሽራ ማንነትና እኛም ክርስቲያኖች በርስዋ ውስጥ ያለንን ስፍራ እናያለን፡፡ 

“እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።”ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:1-6

The Church, the body of Christ, is the most mysterious heavenly bride. In this message, we will see the nature of this amazing bride and our part in the church.

የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት

ከዚህ በታች ያለውን የወንጌል ድምጽ እንዲሰሙ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡

Play Video

ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ከጨለማና ከሙታን ዓለም ተለይተው የወጡ ምእመናን አንድ ሆነው የተሰሩባት የክርስቶስ ኢየሱስ አካልና ሙሽራ ናት፡፡ የልቡናችን ዓይኖች በርተውልን ብናየው እኛ ክርስቲያኖች እጅግ የከበርን ሰዎች ነን፡፡ በእውነተኛይቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዚህ ምድር የምናውቃቸውና በቋንቋና በዘር ልዩነት ሲገፋፉ የሚኖሩ የአሮጌው ዓለም ሰዎች ስፍራ የላቸውም፡፡ የአካሉ የቤተ ክርስቲያን ብልቶች መሆን የሚችሉት ከዚያ ከድሮው ባቢሎናዊ ማንነታቸው በክርስቶስ የመስቀል ሥራ በመዳን ነው፡፡ እውነተኛዩ ቤተ ክርስቲያን እንደኖህ መርከብ ናት፡፡ የኖህ መርከብ በዚህ ምድር ካሉት እንስሳትና አራዊት ሁሉ የተውጣጡ ብዙ እንስሶች በውስጥዋ የነበሩ ቢሆንም አንበሳው በሬውን፤ ነብሩ ፍየልዋን፤ ተኩላው በጉዋን አልበሏቸውም፡፡ የአውሬነታቸው ባህርይ በእግዚአብሔር ኃይል ጠፍቶ እርስ በርስ ሳይጎዳዱ ነው በመርከቢትዋ ውስጥ የነበሩት፡፡ ቤተ እውነተኛዋ ክርስቲያንም አደገኛ አውሬ የሆነው አዳም ወይም አሮጌው ሰው የማይኖርባት ይልቅስ በዳግም ልደት አሮጌ ሰዋቸውን ያወለቁ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከዓለም ጉድፍ የነጹ ሰዎች አንድ ቤተሰብ የሆኑባት ናት፡፡ እንግዲህ ወዳጄ እርስዎም ይህንን ህይወት ይኖሩ ዘንድ በዚህ ትምህርት እግዚአብሔር እየጠራዎት ነው፡፡ የበለጠ መማርና በወንጌሉ ቃል ማደግ የሚወዱ ከሆነ ህልጊዜ ልናገኝዎትና ልናገለግልዎት ዝግጁዎች ነን ይጻፉልን፡፡ እግዚአብሔር ይባርክዎ፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *