የእግዚአብሔር ፍቅር ክፍል ሁለት

የእግዚአብሔር ፍቅር


“ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።” 1. ዮሐንስ 1:7-8

 

በመምህር ጸጋ

ባለፈው መልእክታችን ሰው የሰራቸውን ነገሮች ሁሉ የሰራው ውስን የሆነውን ማንነቱን ይሞሉልኛል ብሎ እንደሆነ አይተን እግዚአብሔር ግን ሙሉና ፍጹም አምላክ ሆኖ ሳለ ይህንን ሁሉ ለምን ፈጠረ? የሚል ጥያቄ አንስተን ነበር፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ እንደሆነና ጉድለቱን ለመሙላት ምንም ነገር መፍጠር እንደማያስፈልገው ከተስማማን በመልኩ የፈጠረንን እኛን ጨምሮ ይህንን ሁሉ ፍጥረት የፈጠረበት ምክን ያት ከቃሉ እንመልከት፤፡

ይህንን በጥቂቱ ለመረዳት በመጀመሪያ ሁለት ነገሮችን አስተውለን መመልከት ያስፈልገናል፡፡ አንደኛው የእግዚአብሔርን ባህርይ ወይም ማንነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሰውን በመልኩ መፈጠር ነው፡፡

ይህ የእግዚአብሔር አንዱ ባህርዩ ነው፡፡ ፍቅር ነው ሲባል እንዲሁ የማእረግ ስም ወይም መጠሪያ ስም ሳይሆን ባህርይ ነው፡፡ ፍቅር ሲባል እንዲሁ የማይንቀሳቀስ ግኡዝ ነገር ሳይሆን እንደ እሳተ ገሞራ በኃይል የሚንቀሳቀስ ኃይል ነው፡፡ ፍቅር ራሱን መሰወር የማይችል ተንቀሳቃሽ ባህርይ ነው፡፡ ፍቅር ራሱን ካልገለጠ መኖር የማይችል ባህርይ ነው፡፡ ፍቅር ገዢ ኃይል ነው፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ባህርይ ሲነገር “ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና” ይለናል፡፡ {1.ዮሐ.4:8}

ይህ የእግዚአብሔር አንዱ ባህርዩ ነው፡፡ ፍቅር ነው ሲባል እንዲሁ የማእረግ ስም ወይም መጠሪያ ስም ሳይሆን ባህርይ ነው፡፡ ፍቅር ሲባል እንዲሁ የማይንቀሳቀስ ግኡዝ ነገር ሳይሆን እንደ እሳተ ገሞራ በኃይል የሚንቀሳቀስ ኃይል ነው፡፡ ፍቅር ራሱን መሰወር የማይችል ተንቀሳቃሽ ባህርይ ነው፡፡ ፍቅር ራሱን ካልገለጠ መኖር የማይችል ባህርይ ነው፡፡ ፍቅር ገዢ ኃይል ነው፡፡  ፍቅር መሪ ኃይል ነው፡፡ ፍቅር ይመራናል ወይም ይነዳናል እንጂ እኛ ፍቅርን አንመራውም፡፡  እግዚአብሔር ደግሞ በፍቅር የሚገዛ ሳይሆን ራሱ ገዢ ፍቅር ነው፡፡ባህርዩ ፍቅር ስለሆነ ይህንን ፍቅር መግለጥ ነበረበት፡፡ ሁሉንም ነገር የሚያደርገው ከዚህ ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ ነው፡፡ የፍቅር ሚስጢር በደንብ ካልገባን እንዴት ከፍቅር ብቻ ተነስቶ ይህንን ሁሉ ይፈጥራል? እንል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከፍቅር የሚበልጥ ምክንያትና ማስወንጨፊያ ኃይል የለም፡፡ ለምሳሌ እኛን ራሳችንን እንደ ምሳሌ ውሰዱ፡፡ ጋብቻ ከመሠረትን በሁላ ቶሎ የሚናፍቀን ልጆች መውለድ ነው፡፡ ለመሆኑ እነዚህን ገና ያልተወለዱ ልጆች እንዴት ነው የምንፈልጋቸው? ማንስ አስገድዶን ነው እጅግ የምንናፍቃቸው? በህግ ተገደን ወይም በሌላ ምክን ያት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ዓይናችንን በዓይናችን እንድናይ የሚናፍቅ የፍቅር ኃይል በውስጣችን ስላስቀመጠ ነው፡፡ ስለዚህ ገና አጭር ይሁኑ ረጅም ወፍራም ይሁኑ ቀጭን የማናውቃቸውን ልጆን በዓይነ ልቡናችን እየሳልን እንናፍቃቸዋለን፡፡ ሳይጸነሱ እንወዳቸዋለን ሳይወለዱ እንናፍቃቸዋልን እናስባቸዋለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በአንድ ስፍራ እንደተናገረው ተፈጥሮስ ስንኳ ያስተምረናል፡፡ {1.ቆሮ 11:14-15}

የአባት ፍቅር

ከዚህ በታች ያለውን የወንጌል ድምጽ እንዲሰሙ በታላቅ ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡

Play Video

ስለዚህ እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነው ባህርዩ በመነሳት የሰውን ልጅ ገና ሳይፈጥረው ሳይሰራው ከመሬት አፈር ሳያበጀው የሕይወትንም እስትንፋስ እፍ ሳይልበት ከዘለዓለም በውስጡ በልቡ ወደደው፡፡ ያ ሰው እኔም አንቺም አንተም እርስዎም መሆናችሁን ስታውቁ በደስታ ትፈነድቃላችሁ፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ቀን ብርሃን ይሁን ብሎ ፍጥረትን መፍጠር ከመጀመሩ በፊት እጅግ የሚወደውን ሰውን በልቡ በፍቅር አቅፎ ይዞት ነበር፡፡ መቼ ነበረና ለምትሉ ቅዱስ ዳዊትን ጠይቁ እንዲህ በማለት ያስተምረናል፤ “አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች። እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም። ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።” መዝ 139:13-16፡፡ አዎ እግዚአብሔር አምላካችን ሳንሰራ አይቶናል፡፡ እንደሰው ከሰራ በኋላ አይደለም ያየን ፡፡ አምላክ  ነውና ሳይሰራን አየን፡፡ ሳንኖር በውስጡ ነበርን፡፡ ስለዚህ እኛን በልቡ ሰውሮ ለኛ የሚያስፈልገውን ሁሉ ይፈጥር ጀመር፡፡ ወላጆች ገና ላልተወለዱ ልጆቻቸው ጥሩ መጫወቻዎችን ልብሶችን እንደሚገዙ እግዚአብሔር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ለሰው ስጦታ አድርጎ የሚሰጣቸውን ፍጥረታት ይፈጥር ጀመር፡፡ ለሰው ልጅ መኖሪያ አገረ መንግሥት አድርጎ ሊሰጣት ያለችው ምድር በምን ሁኔታ ውስጥ እንደነበረች ነቢዩ ሙሴ ሲጽፍልን“ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።” ዘፍ.1:2  እግዚአብሔርም ለምወድው ልጄ ለሰው ልጅ አትመችም ስለዚህ ላሰማምርለት ላስውብለት በእጸዋት በእንስ ሳትና በአበቦች አሳምሬ ላዘጋጅለት ብሎ “ብርሃን ይሁን”  በማለት ጀመረ፡፡ ዘፍ1:3  ይቀጥላል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *