የሳምራዊትዋ ሴት ማስታወሻ
የሳምራዊትዋ ሴት ማስታወሻ ሕይወቴና ታሪኬ ከሰው ጋረ አያስኬደኝምሕይወቴ ውበት የለውምየሰዎች መጠቋቆሚያ ሆኜአለሁትኩር ብየ እንኳ ሰዎችን መመልከት አልችልምበቀትር ሁልጊዜ ምንጩ ባዶ ነበር።ዛሬ ግን አንድ ሰው አገኘሁአለባበሱ የአይሁድ ነውበዚህ ስፍራ ምን ያደርጋል?ኢየሱስ ክርስቶስ ውሀ አጠጪኝ ብሎ ሲጠይቀኝ።እንዴት ውሀ ይለምነኛል?እንኳንስ ውሀ ሊለምነኝ አይሁዳዊ አናግሮኝ አያውቅም።ንዴቴን በሚገልጽ ንግግር መቸም እናንተ አንድ ነገር ካልተቸገራችሁ አታናግሩንምብየ አሰብኩና አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን …